ሃሙራቢ (አካድኛ፤ ከአሞርኛ አሙራፒ) ከ1705 እስከ 1662 ዓክልበ. ድረስ ('ኡልትራ አጭር አቆጣጠር') የባቢሎን ንጉሥ ነበረ። አባቱ ሲን-ሙባሊት ማዕረጉን ከተወ በኋላ ወራሹ ሃሙራቢ የባቢሎንን መንግሥት ግዛት በሜስፖጦምያ በጦርነት አስፋፋ።[1]

የባቢሎን ግዛት መስፋፋት - ከሃሙራቢ መጀመርያ (1705 ዓክልበ.) እስከ መጨረሻው አመት (1662 ዓክልበ.) ድረስ

ሃሙራቢ በተለይ የሃሙራቢ ሕገ ፍትሕ ስለሚባለው የ1704 ዓክልበ. ሕገ ፍትሕ ይታወቃል። ሕግጋቱ የተቀረጹ ቁመቱ 2.4 ሜትር በሆነ ድንጋይ ሲሆን በ1893 ዓ.ም. ለሥነ ቅርስ ተገኝቷል። ሃሙራቢ እንደ ሕግ-ሰጪ ንጉሥ ዝነኛ ስለሚሆን፣ ምስሉ በአሜሪካ መንግስት ቤቶች ዛሬው ሊታይ ይችላል።

 
የሃሙራቢ መንግሥት መስፋፋት - ሌላ አስተያየት። አሦር በይፋ ነጻ ቢሆንም በሃሙራቢ ዘመን ለባቢሎን ተገዥ ሆነ።

ሃሙራቢ የወረሰው ግዛት ባቢሎን ከተማ ብቻ ሳይሆን በአባቶቹ ዘመናት ቦርሲፓኪሽሲፓር ደግሞ በወረራ ተጨምረው ነበር። ጎረቤቶቹ አገራት ግን — ኤሽኑናላርሳኤላምአሦር — ሁሉ ከባድ ሃያላት ነበሩ። በተለይ ወደ ስሜኑ 1 ሻምሺ-አዳድ የአሦርን ዙፋን ይዞ ግዛቱን በጦር እያስፋፋ ነበር።[2] ሽምሺ-አዳድ በ1707 ዓክልበ. ማሪን ይዞ ነበር። ወደ ምስራቁ የላርሳ ንጉሥ ሪም-ሲን በበኩሉ የርሱን ግዛት በጦር እያስፋፋ ነበር። በ1705 ዓክልበ. ሪም-ሲን ኢሲንን ከባቢሎን ያዘው። ሃሙራቢ ግን በ1699 ዓክልበ. ኢሲንንና ኡሩክን ከሪም-ሲን ያዘ። በ1695 ዓክልበ. ማልጊዩምን፣ በ1694 ዓክልበ. ራፒቁምንም ለባቢሎን ግዛት ጨመረ።

በሃሙራቢ 17ኛው አመት (በ1688 ዓክልበ.) ተፎካካሪው ሻምሺ-አዳድ ዐርፎ የሻምሺ-አዳድ ልጅ 1 እሽመ-ዳጋን የአሦርን መንግሥት ወረሰ።

ከዚህ በኋላ፣ ኤላማውያን ኤሽኑናን ወርረው አጠፉት።[3] በ1679፣ ኤላማውያን አሦርን አሸንፈው እሽሜ-ዳጋን ወደ ሃሙራቢ ሸሸ። ኤላም ከባቢሎንና ከላርሳ መካከል ጸብ እንዲጀመር በስውር ሞከረ።[4] ሃሙራቢና ሪም-ሲን ይህን ባወቁ ጊዜ ተባበሩና ኤላምን አሸነፉ።[4] ሪም-ሲን ግን ብዙ እርዳታ መስጠት ባለመቻሉ ሃሙራቢ ተቆጥቶ በላርሳ ላይ ዞሮ በ30ኛው አመት (በ1675 ዓክልበ.) ላርሳን ያዘ። ይህም በላርሳ ላይ የሪም-ሲን 59ኛው አመት ነበረ።[5] በዚህም ሰዓት ሃሙራቢ ኒፑርንም በመያዝ የመስጴጦምያ ዋናና «ቅዱስ» ከተማነት ከኒፑር ወደ ባቢሎን ለዘለቄታ ተዛወረ።

ከዚህ በኋላ በደቡብ ሜስፖጦምያ በሙሉ ሃሙራቢ ገዢ ነበር። ወደ ስሜኑ ዞሮ ኤሽኑናን በ1674 ወረረና ማሪን በ1673 ያዘ። ሱባርቱ (የአሦር ዙሪያ) በብሔራዊ ሁከት ተይዞ የራሳቸውን መሳፍንት ነበሯቸው፣ ሃሙራቢ ግን በዚያ የውነት ባለሥልጣን ሆነ። ከዚህ በላይ በፋርስ ተራሮች ብዙ ጊዜ በጉቲዩምና በ1669 ዓክልበ. በቱሩኩ ሕዝብ ላይ ይዘመት ነበር።

ከዙሪያው ዋና ከተማ-አገሮች መካከል፣ ወደ ምዕራብ በሶርያ የተገኙ ሐላብ (የያምኻድ መንግሥት)ና ቃትና ብቻ በነጻነታቸው ቀሩ። አንድ የሃሙራቢ ሐውልት ግን በጣም ወደ ስሜን በዲያርባክር (የአሁን ቱርክ) ተገኝቷል፤ በዚህ ላይ «የአሞራውያን ንጉስ» የሚል ማዕረግ ይወስዳል።[6]

ሃሙራቢ በ1662 ዓክልበ. ዐርፎ ልጁ ሳምሱ-ኢሉና መንግሥቱን ወረሰው።

የሃሙራቢ ሕግጋት ምሳሌ

ለማስተካከል
  • §7 «ማንም ሰው ብርን ወይንም ወርቅን፣ ወይንም ባርያን ወይንም ገረድን፣ ወይንም በሬን ወይንም በግን ወይንም አህያን ወይንም ማንኛውንም ነገር፣ ከሰው ልጅ ወይም ከሰው ባርያ እጅ ያለ ምስክሮችና ውሎች ቢገዛው ወይም ለአደራ ቢቀብለው ኖሮ፣ ሰውዬው ሌባ ነው፣ ይገደላል።»
(አካድኛ፦ ሹማ አዊሉም ሉ ካስፓም ሉ ሑራጻም ሉ ዋርዳም ሉ አምታም ሉ አልፓም ሉ ኢመራም ሉ ኢሜራም ኡ ሉ ሚማ ሹምሹ ኢና ቃት ማር አዊሉም ኡ ሉ ዋራድ አዊሉም ባሉም ሺቢ ኡ ሪክሻቲም ኢሽታም ኡ ሉ አና ማጻሩቲም ኢምሑር፣ አዊሉም ሹ ሻራቅ ኢዳክ።)

በአሜሪካ አብያተ መንግሥት

ለማስተካከል
 
ከሕግጋቱ በላይ የሚታየው የጥንት ባቢሎናዊ ትርዒት። ሃሙራቢ (ቆሞ) ጽሁፉን ከጣኦቱ ከሻማሽ ሲቀበል።

ዋሺንግተን ዲሲ በአሜሪካ ምክር ቤት ውስጥ በእብነ በረድ ተቀርጸው ከ23 ታሪካዊ ሕግ-ሰጪዎች ምስሎች መካከል የሃሙራቢ ምስል አንዱ ነው።[7]

በአሜሪካ ላይኛ ችሎት ቤት ውስጥ በደቡብ ግድግዳ ላይ ሃሙራቢ ከታሪካዊ ሕግ-ሰጪዎች ጋራ የሚያሳይ ትርዒት አለ።[8]

ቀዳሚው
ሲን-ሙባሊት
ባቢሎን ንጉሥ
1705-1662 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሳምሱ-ኢሉና

ግርጌ ነጥቦች

ለማስተካከል
  1. ^ Beck, Roger B.; Linda Black, Larry S. Krieger, Phillip C. Naylor, Dahia Ibo Shabaka, (1999). World History: Patterns of Interaction. Evanston, IL: McDougal Littell. ISBN 0-395-87274-X. OCLC 39762695. 
  2. ^ Van De Mieroop 2005, pp. 3–4
  3. ^ Van De Mieroop 2005, p. 17
  4. ^ Van De Mieroop 2005, p. 18
  5. ^ Van De Mieroop 2005, p. 31
  6. ^ Clay, Albert Tobias (1919). The Empire of the Amorites. Yale University Press. pp. 97. 
  7. ^ "Hammurabi". Architect of the Capitol. በ2008-05-19 የተወሰደ.
  8. ^ "[[[:መለጠፊያ:SCOTUS URL]] Courtroom Friezes]". Supreme Court of the United States. በ2008-05-19 የተወሰደ.

ዋቢ መጻሕፍት

ለማስተካከል

የውጭ መያያዣዎች

ለማስተካከል
 
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ሃሙራቢ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።
  NODES
Note 1