አፍሪቃ (አፍሪካ) ከዓለም ሁለተኛ ትልቅ አህጉር ነች። ከ1,869 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በዚች አህጉር የሚኖር ሲሆን በጠቅላላ 56 ሀገሮች ይገኛሉ። ከእነዚህም ሀገሮች መሀል ናይጄሪያ በህዝብ ብዛት (127 ሚሊዮን) የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ፤ ግብፅኢትዮጵያ በ126 ሚሊዮን እና በ120 ሚሊዮን ህዝብ በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ከሌሎች የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ጋር በመደማመር ድህነትን በማባባስ ደረጃ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡

አፍሪቃ

ስፋት 30,221,532 ካሬ ኪ.ሜ.
ሕዝብ ብዛት 522,011,000[1] (1997 ዓ.ም., 2ኛ)
Density 30.51 በካሬ ኪ.ሜ.
ሀገሮች
በጥገኝነት
መጠሪያ ስም አፍሪቃዊ
ቋንቋዎች የአፍሪቃ ቋንቋዎች እና ሌሎች
ሰዓት ክልል UTC-1 (ኬፕ ቨርድ) እስከ UTC+4 (ሞሪሸስ)


ጂዎግራፊና ሕዝብ

ለማስተካከል

ከስድስቱ ዓለማት አንዱ አፍሪካ ነው። አፍሪካ ሰፊ ነው። የዓለምም አራተኛ ክፍል ይሆናል። ከኤውሮጳ የሚለየው በሜዴቲራኒያን ባሕር ነው። ከአሜሪካም በአትላንቲክ ውቅያኖስ ይለያል። ከኒው ዮርክም ቢሆን ወይም ከቦስቶን ከአሜሪካ የሚቀርበው ክፍል ሦስት ሺህ ማይል ይሆናል። ነገር ግን በጊብሮልታር (ጂብራልታር) 0ኩል የሆነ እንደ ሆነ ለኤውሮጳ በጣም ቅርብ ነው።

እስያኤርትራ ባሕር ይለያያል። የሆነ ሆኖ እስያ ባንድ ወገን ሱዝ ካናል በሚባለው በኩል ከአፍሪካ ጋር ተጋጥሞአል። ሙሴ ሌስፖስ መርከብ እንዲተላለፍ ብሎ አስቆፍሮ ያስከፈተው በዚህ በኩል ነው።

አፍሪካ ከሌላው ዓለም ይልቅ የታወቀው በጣም ትንሽ ነው። ኤውሮጳውያን ደኅና አድርገው አፍሪካን አልመረመሩትም። ከሕዝቡ የሚበልጡት ሻንቅሎች ናቸው። ከነዚህም ብዝዎቹ በነገድ የተለያዩ ናቸው።

ዓየሩ ሙቀት ያለው ስለ ሆነ፣ ለመጠጊያቸው የሚፈልጉት ትንሽ ጎጆና ትንሽ ልብስ ነው። ስለዚህ ቤታቸው የተዋረደ ነው። ቅጠላቅጠሉን ጎጆ ሠርተው በትንሽ ቤት ይኖራሉ። መቸውንም ልብሳቸው አንዲት ቁራጭ ጨርቅ ናት፤ በወገባቸውም ይጠመጥሟታል።

ከሻንቅሎቹ በቀር ደግሞ ሌሎች አያሎች የአፍሪካ ዘሮች አሉ። ከግብፅ ጀምሮ እስከ ሐበሻ ድረስ ያሉት ባላገሮች የጥንት ግብፃውያንነታቸውን ሳይለቁ ከቱርኮችና ከዐረቦች ከሌሎችም የተቀላቀሉ ናቸው።

ሰሐራ የሚባለውን ልክ የሌለውን በረሃና በዙሪያው ያለውን አውራጃ ሁሉ ጨምረው ፈረሶቻቸውንና ግመሎቻቸውን ይዘው ለማሰማራት ወይም ለመዝረፍ ከአንዱ ወዳንዱ የሚዞሩ አረቦች ይዘውታል።

አፍሪካ በመላው ወደ ሥልጣኔ ያልደረሰ ነው ተብሎ ይታሰባል፤ ከሕዝቡ የሚበዙት እስላሞች ናቸው።

በመካከለኛው አፍሪካ አንበሳዝሆንአውራሪስየሜዳ አህያና ሌሎችም አራዊት ይገኙበታል። በደኑ ሁሉ ጦጣዝንጀሮ ይንጫጩበታል። በጫካው ውስጥ ዘንዶሰጎን ሞልተዋል። በሜዳው አጋዘንድኩላየሜዳ ፍየል ተሰማርተው ይታያሉ። በየወንዙና በየባሕሩ ጎማሬ ይታያል። አዞ በረጋ ውሃ ውስጥ ትኖራለች። አዕዋፍም በየስፍራው ሁሉ ይታያሉ።



የዓለም አሁጉሮች
 
አፍሪቃ
 
እስያ
 
አውሮፓ
 
ኦሺያኒያ
 
ሰሜን አሜሪካ
 
ደቡብ አሜሪካ
 
አንታርክቲካ
ስሜን አሜሪካ|

አንታርክቲካ| አውሮፓ| አውስትሬሊያ| አፍሪቃ| እስያ| ደቡብ አሜሪካ

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  1. ^ "World Population Prospects: የ 2006 እ.ኤ.ኣ. ዕትም" Archived ሜይ 11, 2011 at the Wayback Machine United Nations (Department of Economic and Social Affairs, ሕዝብ ክፍል)
  NODES
Note 1