ኤብላሶርያ ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው በአረብኛ ተል ማርዲኽ ተብሎ የኤብላ ጽላቶች የተገኙበት ፍርስራሽ ነው።

ኤብላ
(ተል-ማርዲኽ)
የኤብላ ፍርስራሽ
ሥፍራ
ኤብላ is located in Syria
{{{alt}}}
ዘመናዊ አገር ሶርያ

አካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን አስቀድሞ በሆነው ዘመን ኤብላ ሰፊ መንግሥት በሶርያ ዙሪያ እንደ ነበረው ይታወቃል። የጽላቶች ቤተ መዝገብ ሕንጻ የተቃጠለበት ጊዜ የሚከራከር ነው። ሦስት ዋና አስተያየቶች አሉ፤ 1) ከሳርጎን በፊት በኤብላ ተፎካካሪ በማሪ፤ 2) በሳርጎን እራሱ፤ ወይም 3) በሳርጎን ልጅ ልጅ በናራም-ሲን። አሁን በሳርጎን ዘመን በ2074 ዓክልበ ግድም እንደ ጠፋ ቢመስልም በሳርጎን ወይም በማሪ ሰዎች እጅ መጥፋቱን እርግጠኛ አይደለም።

የኤብላ ጥንታዊ መንግሥት

ለማስተካከል

ኤብላ መቼ እንደ ተመሠረተ ባይታወቅም ምናልባት 2400-2350 ዓክልበ. (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) እንደ ሆነ ሊገመት ይቻላል። የሥነ ቅርስ ሊቃውንት ግን እስከ 3000 ዓክልበ. ድረስ ይገፉታል።

በአንዱ ጽላት ላይ ከኢግሪሽ-ሐላብ (2127 ዓክልበ. ግድም) አስቀድሞ የገዙት ፴ ነገሥታት ስሞች ይዘረዝራሉ፦ ሳኩሜ፣ ሹ-[...]፣ ላዳው፣ አቡጋር፣ ናምነላኑ፣ ዱሙዳር፣ እብላ፣ ኩልባኑ፣ አሻኑ፣ ሳሚዩ፣ ዚያሉ፣ ሩማኑ፣ ናማኑ፣ ዳ-[...]፣ ሳጊሹ፣ ዳኔዩም፣ ኢቢኒ-ሊም፣ ኢሽሩድ-ዳሙ፣ ኢሲዱ፣ ኢሽሩድ-ሐላም፣ ኢክሱድ፣ ሪዳ-ሊም፣ አቡር-ሊም፣ አጉር-ሊም፣ ኢቢ-ዳሙ፣ ባጋ-ዳሙ፣ ኤናር-ዳሙ፣ ኢሻር-ማሊክ፣ ቁም-ዳሙ፣ እና አዱብ-ዳሙ ናቸው።

ከነዚህ ስሞች ብዙ በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶቻቸው ደግሞ ይገኛሉ፣ በተለይም ከ«ሳጊሹ» እስከ «ኢሽሩድ-ዳሙ»፣ እና «ኤናር-ዳሙ» ያሉት ስሞች ይጠራሉ። ኢቢ-ዳሙ በካነሽ ሐቲ ከተገኘ ማኅተም ቅርስ ይታወቃል። ቁም-ዳሙ ከሌሎች ሰነዶች ሲታወቅ ከማሪ መንግሥት ጋራ የሆኑት ችግሮች በእርሱ ዘመን እንደ ጀመሩ ይመስላል። ይህም በማሪ ነገሥታት ሳዑሙ ወይም ኢቱፕ-ኢቫር ዘመናት እንደ ነበር ይታሥባል። ተከታዩም አዱብ-ዳሙ እጅግ አጭር ዘመን እንደ ነገሠ ይታወቃል።

 
የኤብላ መንግሥት በጫፉ በ2109 ዓክልበ. ግድም (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር)

የተገኙት መዝገቦች ከአዱብ-ዳሙ በኋላ ከገዙት ከሦስቱ መጨረሻ ነገሥታት ዘመኖች ናቸው። እነርሱም ኢግሪሽ-ሐላብ (12 ዓመታት)፣ ኢርካብ-ዳሙ (7 ዓመታት) እና ኢሻር-ዳሙ (35 ዓመታት) ናቸው (2127-2074 ዓክልበ.)። ከሃይለኛ ጠቅላይ ምኒስትሮቻቸው የሚታወቁ አራኩምኤብሪዩም እና ኢቢ-ዚኪር (ወይም ኢቢ-ሲፒሽ) ናቸው። መዝገቦቹ የተጻፉበት ኩኔይፎርም በተባለ ጽሕፈት ሲሆን ቋንቋቸው ኤብላኛ ነው፣ ይህ ለአካድኛ ተመሳሳይ የሆነ ሴማዊ ቋንቋ ወይም ቀበሌኛ ነው።

ኢሻር -ዳሙ በማሪ ላይ ከናጋርና ከኪሽ ጋራ ስምምነት ተዋዋለ፤ አለቃውም ኢቢ-ዚኪር የማሪን ሃያላት በተርቃ ውግያ አሸነፋቸው። ከዚህ በኋላ የኤብላ ሥራዊት አርሚን ያዙ፣ የኢቢ-ዚኪርም ልጅ ኤንዚ-ማሊክ እዝያ ገዥ ተደረገ። ኢሻር-ዳሙ ካረፈ በኋላ ግን ምናልባት 2074 ዓክልበ. ግ. ሳርጎን ወይም ማሪ ኤብላን እንዳጠፋ ይመስላል።

ከዚህ በኋላ ኤብላ እንደገና እንደተሠራ ይታወቃል። በላጋሽ ንጉሥ ጉዴአ ዘመን (2009-1989 ዓክልበ.) በአንዱ ሰነድ ጉዴአ የአርዘ ሊባኖስን ዕንጨት ከኤብላ ግዛት ከኡርሹ ይጠይቃል። በኡር ንጉሥ አማር-ሲን ፯ኛው ዓመት (1912 ዓክልበ.) የኤብላ ንጉሥ ይጠቀሳል። ከዚህም በኋላ ኤብላ ሁለተኛ ምናልባትም በሑራውያን ዕጅ እንደ ጠፋ ይታሥባል።

ዳግመኛም ተሠርቶ በሦስተኛው የኤብላ መንግሥት ወቅት፣ የንጉሥ ኢቢት-ሊም ሐውልት ቅርስ ተገኝቷል፤ ልክ መቼ እንደ ነገሠ ግን ገና እርግጠኛ አይደለም። የኤብላ ንጉሥ ኢመያግብጽ ፈርዖን ሆተፒብሬ ዘመን (1806-1803) እንደ ገዛ ከአንድ ሐውልት ቅርስ ታውቋል። በያምኻድ መንግሥት ዘመን ለያምኻድ ተገዥ ነበረ፤ የአላላኽ ገዥ አሚታኩም ልጅ የኤብላን ልዕልት አገባ። የኬጥያውያን መንግሥት ንጉሥ 1 ሙርሲሊ በ1508 ዓክልበ. ግ. ኤብላንም ያምኻድንም አጠፋቸው። በዚያን ጊዜ የኤብላ መጨረሻ ንጉሥ ኢንዲሊማ ተባለ።

ከዚያ በኋላ በሥፍራው ላይ ጥቃቅን መንደር ብቻ ቀረ፣ ይህም ምናልባት እስከ 500 ዓ.ም. አካባቢ ድረስ ቆየ።

  NODES
Done 1