ኡር (ሱመርኛኡሪምአካድኛኡሩ) በደቡብ ሱመር (የዛሬይቱ ኢራቅ) የነበረ ከተማና መንግሥት ሲሆን በኤፍራጥስ ወንዝ ደቡብ ዳርቻ ላይ ተገኘ። በጥንት ሥፍራው በፋርስ ወሽመጥ ላይ ሲሆን አሁን ግን ባሕሩ የብስ ሆኖ ከወሽመጡ በጣም ይርቃል።

ኡር ከተማ በደቡብ ሱመር

ኩፋሌ 10፡24 መሠረት «የከለዳውያን ዑር» በአርፋክስድ ወገን በኬሴድ ልጅ በዑር ተሠርቶ ነበር፤ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ አብርሃም የተወለደበት ከተማ ነው። የሥነ ቅርስ ሊቅ ሌዮናርድ ዉሊ «የከላውዴዎን ኡር»ና በኤፍራጥስ ላይ የነበረው ዑር ሱመር አንድላይ እንደ ነበሩ የሚያምን ቢሆን፤ በቀድሞው አይሁድና አረብ ልማድ ግን «የከላውዴዎን ኡር» በስሜን መስጴጦምያ እንደ ተገኘ ይላል።

ኡር እጅግ ጥንታዊ መሆኑ ይመዘገባል። የዱሙዚድ ሕልም በተባለ ትውፊት፣ የኡሩክ ንጉሥ ዱሙዚድ ከቅንጦቱ በተገለበጠው ጊዜ፣ ያባረሩት አመጸኛ ረሃብተኞች ከኡርና ከሌሎች የሱመር ከተሞች እንደ መጡ ይነግረናል። በኡር ፍርስራሽ ውስጥ፣ የከተማው መጀመርያ ነገሥታት መቃብሮች ተገኝተዋል፤ ከነኚህም ውስጥ የንጉሦች አካላምዱግመስካላምዱግ፣ የንግሥት ፑአቢም መቃብሮች አሉ። የመስካላምዱግ ልጅ ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ኡሩክ፣ ኪሽኒፑርን ይዞ የሱመርን ላዕላይነት ለኡር መንግሥት መሰረተ። ይህ የኡር 1ኛው ሥርወ መንግሥት ይባላል። በዚህ ስርወ መንግሥት መጨረሻ፣ ኡር ድል ሆኖ ሥልጣኑ ወደ ኤላም ከተማ ወደ አዋን እንደ ተወሰደ በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ላይ ይተረካል።

በ22ኛ ክፍለ ዘመን ዓክልበ. የኡር 2ኛው ሥርወ መንግሥት ነገስታት ናኒ እና መስኪአጝ-ናና በሱመር ላዕላይነት ገዙ፤ ስለዚህ ሥርወ መንግሥት ግን ብዙ አይዘገብም፤ የአዳብ መንግስት በንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ ሥር ተከተለው። ከአካድ መንግሥትና ከጉታውያን ግዛት በኋላ በሆነ ዘመን፣ ዝነኛ የሆነ የኡር 3ኛው ሥርወ መንግሥት ተነሣ። መጀመርያው ንጉሡ ኡር-ናሙ የኡር-ናሙ ሕግጋትን (1983 ዓክልበ.) አወጣ።

በዚህ ታላቅ የኡር መንግሥት መጨረሻ ወቅት አገሩ በረሃብ፣ በአውሎ ንፋስና በጦርነት ተፈተነ። አሞራውያን የተባለው ሕዝብ በብዛት በሱመር ውስጥ ሠፍሮ ነበር። ኢሲን የተባለው ከተማ ከኡር ነጻ ወጥቶ ለራሱ ራስ-ገዥ መንግሥት ሆነ። በመጨረሻ (1879 ዓክልበ.) የኡር ጠላቶች ኤላማውያን ኡርን ዘርፈው አጠፉት፤ ከዚያ በኋላ የኡር ሥልጣን ወድቆ ኢሲን ከተማ የደቡብ መስጴጦምያ ዋና ሥልጣን ሆነ።

የኡር ነገሥታት

ለማስተካከል

(ኡልትራ አጭር)

የኡር 1ኛ መንግሥት

ለማስተካከል

የኡር 2ኛ መንግሥት

ለማስተካከል

የኡር 3ኛ መንግሥት

ለማስተካከል
  NODES
Note 1