ሁጎ ራፋኤል ቻቬዝ ፍሪያስ ፶፪ኛ የቬኔዝዌላ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ከ1954 እስከ 2013 እ.ኤ.አ. የኖረ የቬንዝዌላ መሪ ሲሆን በጸረ-ኢምፔርያሊስት አቋሙና የቬንዝዌላን የነዳጅ ሀብት ድሆችን ለመደጐም በማዋል ከፍተኛ እውቅና አግኝተዋል።ሁጐ ቻቬስ በማርች 2013 በሞት ቢለዩም በጸረ-ኢምፔሪያሊስት አቋማቸው የቬንዝዌላ ህዝብና የአለም መሪ አድርገው የሚያዩአቸው ጥቂት አይደሉም። /የአሜሪካ ጠላት ተሰናበተ/ ያሉት በአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን አዕምሮአቸው/ የታጠበባቸው/ሰዎች እንጂ ቻቬዝ የአሜሪካ ጠላት ሳይሆኑ የዋሽንግተን ኢ-ፍትሃዊነት፤በውሸትና በወታደራዊ ወረራ፤በቦምብ በመደብደብና በጠብ ጫሪነት የተዋቀረው የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ጠላት ነበሩ በማለት ይገልጿቸዋል።ቻቬዝ በአቋማቸው በምእራባውያን መሪዎች ቢጠሉም በቻይና፤ በሩስያ፤በብራዚልና በሌሎችም ሀገሮች የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ተሰጥቶአቸዋል።ቻቬዝ ከነዳጅ በሚገኘው ገቢ የናጠጡ ሀብታም ሊሆኑና የአሜሪካ አሻንጉሊት በመሆን ክብር ሊያገኙ ይችሉ ነበር። ከዚህ ይልቅ ከነዳጅ የሚገኘው ገቢ ለዝቅተኛው መደብ እንዲደርስ በማድረግ ለሶስት ጊዜ እንደተመረጡት የኢኳዶር ፕሬዝደንት ራፋኤል ኮሬያ ፤ ከአሜራካ በተቃራኒ በመቆም ለጁልያን አሳንጌ የፖለቲካ ጥገኝነት እንደሰጡት ኤቮ ሞራሌስ እውነተኛ መሪ እንደሆኑ የቬንዙዌላ ህዝብ ተቀብሎአቸዋል ይላሉ። የቬንዝዌላ ህዝብ እየወደዳቸው በሄደ ቍጥር የምእራቡ ፖለቲካና መገናኛ ብዙሀን ሴጣን ሊያስመስሏቸው ጥረዋል።ከዋሽንግተን በተቃራኒ መቆም ዋጋያስከፍላል።በ2002 በሲ አይ ኤ ተቀነባብራል የሚባል የመንግስት ግልበጣ ተሞክሮባቸዋል።

ሁጎ ቻቬዝ
  NODES
HOME 1
languages 1
Note 1
os 2