==

ሃትሸፕሱት
የሃርሸፕሱት ሐውልት
የሃርሸፕሱት ሐውልት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1487-1466 ዓክልበ.
ቀዳሚ 2 ቱትሞስ
ተከታይ 3 ቱትሞስ
ባለቤት 2 ቱትሞስ
ሥርወ-መንግሥት 18ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት 1 ቱትሞስ

==


ሃትሸፕሱትጥንታዊ ግብጽግብጽ አዲስ መንግሥትና የ18ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ስትሆን ምናልባት 1487-1466 ዓክልበ. የገዛች ነበረች።

ከዚያ በፊት የ2 ቱትሞስ ንግሥት እና ያባቱ 1 ቱትሞስ ልጅ ነበረች። የ2 ቱትሞስ ቁባት ንግሥት ኢሰት ተባለች፣ እርሷም የተከታዩ 3 ቱትሞስ እናት ሆነች። የ፪ ቱትሞስ ተከታይ በይፋ ልጁ ፫ ቱትሞስ ሲሆን፣ እሱ ግን ገና የ 2 ዓመት ሕጻን ልጅ ሆኖ የቱትሞስ ንግሥት ሃትሸፕሱት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴው፣ በቅርብም ጊዜ ውስጥ በራስዋ መብት ፈርዖን ተባለች። በ22ኛ ዓመትዋ (1466 ዓክልበ. ግ.) ዓርፋ ያንጊዜ ፫ ቱትሞስ ለብቻው ፈርዖን ሆነ።

22 አመት ገዛች የሚታሠበው ከሺህ በላይ አመት በኋላ በኖረው በማኔጦን ምስክር ነው። በርሱ ዝርዝር በዚህ ሥፍራ አመንሲስ ወይም አሜሲስ የተባለች ንግሥት ለ22 ዓመት (እንደ አፍሪካኑስ ቅጂ) ወይም ለ21 ዓመት 9 ወር (እንደ ዮሴፉስ) ገዛች ይላልና። በ3 ቱትሞስ 22ኛው ዓመት በሶርያ እንደ ዘመተ እንሰማለን፣ ስለዚህ እንደሚታስበው የሃትሸፕሱት 22ኛ አመት በይፋ ደግሞ የ፫ ቱትሞስ 22ኛ ዓመት ተባለ፣ እርሱ በሕጻንነቱ በእንጀራ እናቱ ዘመን በይፋ ፈርዖን ተብሎ ነበርና።

በአንድ ጽላት ደግሞ በየካቲት 10 ቀን፣ 22ኛ ዘመነ መንግሥትዋ አረፈች የሚል ነው። ፈርዖን የሆነችም ግንቦት 4 ቀን፣ 1ኛ ዘ. መ. ስለሚታወቅ፣ ልክ ማኔጦን እንዳለው 21 ዓመት 9 ወር ገዛች ማለት ነው።

በሃትሸፕሱት ፱ኛዋ ዓመት ወይም 1479 ዓክልበ. አምስት መርከቦች ወደ ፑንትንግድ እንደ ላከች ይታወቃል።

በሃትሸፕሱት ዘመን በርካታ ሃውልቶች ተሠሩ። ወደ ፫ ቱትሞስ ዘመን መጨረሻ፣ ልጁ 2 አመንሆተፕ የጋራ ፈርዖን በሆነበት ጊዜ (1435 ዓክልበ.) ወደያው ብዙ የሃትሸፕሱት ምስሎችና ካርቱሾች ከቅርሶቹ ለመደምሰስ እንደ ጣረ ይመስላል። የዘመንዋን ትዝታ ከታሪክ ለማጥፋት እንዳሠበ ይመስላል። ከተረፉት ምስሎቿ ብዛት የተነሣ ግን ዘመንዋን ማጥፋቱ ስኬታም እንዳልሆነ ግልጽ ነው።

ቀዳሚው
2 ቱትሞስ
ግብፅ ፈርዖን
1487-1466 ዓክልበ.
ተከታይ
3 ቱትሞስ
  NODES
Note 1