ሃንጉል (ኮሪይኛ፦ 한글) በተለይ ኮሪይኛ የሚጻፍበት ጽሕፈት ነው። የተፈጠረው በንጉሥ ታላቁ ሴጆንግ1435 ዓም ነበረ። ከዚህ በፊት የቻይና ጽሕፈት ይጠቀም ነበር።

«ሃን-ጉል» በሃንጉል ጽሕፈት

የእያንዳንዱ ክፍለ-ቃል ፊደላት አንድላይ በአንድ ክምር ይጻፋሉ እንጂ እንደ ሌላ አልፋቤት ፊደሎቹ አንድ በአንድ አይጻፉም።

አንዳንዱ ተነባቢ በክፍለ-ቃል መጨረሻ ሊቆም ይችላል፤ ሆኖም ድምጹ ብዙ ጊዘ እታች እንደሚመለከት ይለወጣል። ጽሕፈቱ በአማርኛ አቡጊዳ ውስጥ የማይለዩ ድምጾችን ይለያቸዋል፤ ስለዚህ አያሌ ድምጾች ለብዙ ፊደሎች ምልክቶች ይታያሉ።

ተነባቢ ፊደላት
ድምጽ መጀመርያ
መጨረሻ ንግ
አናባቢ ፊደላት
ድምፅ ኡዊ

ያው ገበታ ዘመናዊው የደቡብ ኮርያ ፊደላት ቀደም-ተከተል የሚያሳይ ነው። በስሜን ኮርያ የሚገኘው እንዲሁም በድሮ ልማዳዊ የሆኑት ቀደም ተከተሎች ይለያያሉ። በጊዜም ላይ ከ1435 ዓም በኋላ አንዳንድ ለውጦች ይደረጉበት ነበር፣ አዳዲስ ምልክቶች ተጨመሩ ወይም የቆዩት ምልክቶች ተተዉ።

በአንድ መላ ምት ዘንድ፣ የሃንጉል መሠረታዊ ተነባቢ ምልክቶች መነሻ በ1261 ዓም በሞንጎሊያ ከተደረጀው ጳግስፓ አቡጊዳ ተጽእኖ ነበረ። ይህም ከቲበትኛ አቡጊዳ፣ እሱም ከሕንድ ብራህሚ አቡጊዳ የተወለደ ሲሆን፣ የዚህም መነሻ ከአረማይስጥ አልፋቤት ስለ ታሠበ ምናልባት ሃንጉል ከቅድመ-ሴማዊ የደረሱት ጽሕፈቶች ትውልድ መካከል ሊቆም ይችላል።

ከኮሪይኛ ውጭ፣ አንዱ ቋንቋ በባው-ባው ከተማ፣ ኢንዶኔዥያ የሚነገረው ቺአ-ቺአኛ ቋንቋ ከ2001 ዓም ጀምሮ በአንዳንድ ሰዎች በሃንጉል ተጽፏል። በ2004 ዓም ግን፣ ባው-ባው ከተማ ሃንጉልን ለቺአ-ቺአኛ ይፋዊ ለማድረግ የነበረውን ዕቅድ ለጊዜው ተወው።

  NODES
Note 1