ተላላፊ በሽታ ማለት በተለያየ መንገድ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመት ህመም ማለት ነው። የሚዛመትበት መንገድ በቀጥታ ወይም ቀጥታ ባልሆነ ንኪኪ ሊሆን ይችላል።[1]

ተላላፊ በሽታዎች ፣የሚከሰቱት እንደ ባክቴሪያዎች, ፈንገሶች እና ቫይረሶች ባሉ አነስተኛ ፍጥረታት ነው። ብዙ አይነት አነስተኛ ፍጥረታት በሰው ላይ ተጠግተው የሚኖሩ ሲሆን አብዛኞቹ ምንም ጉዳት ሳይስከትሉ ይኖራሉ። በአንጻሩ ደግሞ የተቀሩት ለተለያየ በሽታ ይዳርጋሉ።[2]

በጣም ከሚታወቁት ተላላፊ በሽታዎች መካከል እንደ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛ ፣ ኮቪድ-19ኢቦላ ፣ ሄፓታይተስ ፣ ኤችአይቪ/ኤድስ ፣ ሂውማን ፓፒሎማቫይረስ ኢንፌክሽን ፣ ፖሊዮ እና ዚካ ቫይረስ ተጠቃሽ ናቸው። [3]

በሕዝብ ጤና ላይ ያለው ተጽእኖ

ለማስተካከል
 
ይህ ክሊኒክ የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል አሉታዊ ክፍል ግፊት ይጠቀማል።

አብዛኛው ወረርሽኞች በተላላፊ በሽታዎች አማካኝነት ይከሰታሉ። በመሆኑም ሰፊ ወረርሽኝ እንዳይከሰት እና ብዙሀን እንዳይጎዱ በተላላፊ በሽታዎች የተጠቁ ታማሚዎችን ለህሙማን በተዘጋጀ የህክምና ማቆያ ክፍሎ ከሌላው ህዝብ ተለይተው እንዲቆዩ ይደረጋል።ይህም የማህበረሱን ጤንነት ለመጠበቅ የሚደረግ የጥንቃቄ መንገድ ነው። [4] 

  1. ^ "Contagious Disease | NIH" (በen).
  2. ^ "Infectious diseases-Infectious diseases - Symptoms & causes" (በen).
  3. ^ "Infectious Diseases - NFID".
  4. ^ "How To Prepare For Emergencies" (በen). “A primer from the CDC on quarantine and its uses against contagious disease spread”
  NODES
Note 1