ትግርኛኢትዮጵያና በኤርትራ የሚነገር የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ አባል ነው። ትግርኛ በኢትዮጵያ የብሄረ ትግራይ ( ተጋሩ ) ኣፍ መፍቻና 3ኛ ከፍተኛ የተናጋሪ ቁጥር ያለዉ ቋንቋ ሲሆን በኤርትራ ደግሞ የብሔረ ትግርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ነው:: የቋንቋው ተናጋሪዎች ከ11 ሚሊዮን በላይ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ፣ ከዚህ ውስጥ ከ8 ሚሊዮን በላይ በትግራይና በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚነገር ሲሆን በኤርትራ ከ3 ሚሊዮን በላይ ተናጋሪዎች እንዳሉት ይገመታል:: በኤርትራ የአገሪቱ የሥራ ቋንቋና ኣብዛኞቹ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደ መግባብያ የሚጠቀሙበት ቋንቋ ነው::

ትግርኛ ቋንቋ የግዕዝን ፊደል የሚጠቀም ሲሆን በ ኤርትራ አሁን ብሄረ ትግርኛ በመባል የሚታወቀው የሦስቱ አውራጃዎች ማለትም የሓማሴን: ሰራየ ና ኣከለጉዛይ ሕዝብ የሚጠቀሙበት ሕጊ-እንዳባ የተባለው የህግ ስርዓት ተጽፎበት የሚገኝ ሲሆን የመጀመርያዉ የቋንቋዉ ጽሁፍ ደግሞ ሕጊ ኣድግና ተገለባ የሚባለዉ የኣከለጉዛይ ሕገ ስርዓት ነዉ[1]

የትግርኛ ቀለሞች በዓማርኛው ላይ ጥቂት ተጨማሪ ኣሏቸው እንጂ የተቀራረቡ ናቸው። ኣንዳንድ ፀሓፊዎች ግን ከትግርኛ ቀለሞች ውስጥ እነ ""፣ ""፣ ""፣ "" እና "" የራብኦቻቸው ሞክሼዎች መስለዋቸው ተሳስተው ሊቀንሷቸው ኣጥቁረዋቸዋል። እንደ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ገለጻ ግን ሆሄያቱ ሞክሼዎች ስላልሆኑ መብታቸው መከበር ኣለበት ነው።

ደግሞ ይዩ

ለማስተካከል

የውጭ መያያዣዎች

ለማስተካከል
 
Wikipedia
  1. ^ Negash, Abraham, The Origin and Development of Tigrinya Publications, Santa Clara, California2019 p.3 
  NODES
Note 1