አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ



አቡጊዳ ታሪክ

አልፍ (ወይም አሌፍ) በአቡጊዳ ተራ መጀመርያው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች መጀመርያው ፊደል አሌፍ ይባላል። በዓረብኛ ፊደል ደግሞ መጀመርያው ፊደል አሊፍ ሲሆን በግሪክአልፋ ይባላል።

በመጀመርያ በግዕዝ የዚህ ምልክት ምክንያት ተፈናጣሪ ተናባቢ ድምጽ ለማመልከት ነበር። ይህ ድምጽ ፍች «ነዛሪ የጉሮሮ እግድ» ይባላል።[1] በዛሬው አማርኛ ግን ምንም ተናባቢ ሳይኖር አናባቢ ብቻ ሊያመለከት ይችላል። (በዘመናዊ ዕብራይስጥም «አሌፍ» እንዲህ ይጠቅማል።) በዚህ ጥቅም በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከዐይን (ዐ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል።

በአረብኛ ደግሞ «አሊፍ» ከጥንት ተፈናጣሪ ተናባቢ ድምጽ ነበር። በኋላ ግን 'አ' የሚለውን አናባቢ ብቻ ሊያመልከት መጣ። ስለዚህ ነዛሪ የጉሮሮ እግድ ለመጻፍ ሌላ አዲስ ፊደል «ኅምዛ» ተፈጠረ።

በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (አ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ«ኸ» አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ኣ) አንድላይ ነው። ቢሆንም አንዳንዴ በባዕድ ቃላት ይህ አናባቢ በቃል መጀመርያ ሲጋጠም «ኧ» የሚለው ልዩ ፊደል አለ።

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
F1
   


የአልፍ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበሬ ራስ ስዕል መስለ። በዘመናዊ ዕብራይስጥም እስካሁን «አሉፍ» ማለት «ከብት» ማለት ነው። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ «ኢሕ» ነበር።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
    א  


የከነዓን «አሌፍ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «አሌፍ» የአረብኛም «አሊፍ» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «አልፋ» (Α α) አባት ሆነ, እሱም የላቲን አልፋቤት (A a) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የአልፍ ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፩ ከግሪኩ α በመወሰዱ የ«አ» ዘመድ ነው።

  1. ^ "የግዕዝ መረጃ ከኢኦተቤ ማህበረ ቅዱሳን". Archived from the original on 2014-10-13. በ2015-04-22 የተወሰደ.
  NODES
Note 1