ወር
የጊዜ አሀድ
ወር በጊዜ አቆጣጠር በአመት ውስጥ አንድ ክፍፍል ነው።
በአማካኝ አንድ ወር ፴ ቀን ይሆናል። በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከአስራ ሁለት ወራት እያንዳንዱ ፴ ቀኖች ይዞ የተረፉት አምስት ወይም ስድስት ቀናት በ13ኛው ወር ጳጉሜ ይከተታሉ። በጎርጎርያን ካሌንዳር አስራ ሁለት ወሮች እያሉ በእርዝማኔያቸው የሚለያዩ ናቸው።
በአንዳንድ ሌላ ባህል መቆጠሪያ የወር እርዝማኔ በጨረቃ ወቅት (ሃያ ዘጠኝ ቀን ብቻ) ይከተላል፣ ለምሳሌ የአይሁድ አቆጣጠር ወይም የእስላም አቆጣጠር እንዲህ ናቸው። ይህ «ጨረቃዊ አቆጣጠር» ሲባል፣ ጨረቃን ቸል የሚለው መጀመርያው አይነት «ፀሃያዊ አቆጣጠር» ይባላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |