የቅርጫት ኳስ ወይም ባስኬትቦል በዓለም ዙሪያ በቡድኖች የሚጫወት የኳስ እስፖርት ነው። ጨወታው በ1885 ዓም በካናዳዊው ዶ/ር ጄምስ ነይስሚስአሜሪካ አገር ተፈጠረ።

ኳስ በቅርጫቱ በኩል ሲወድቅ
የቅርጫት ኳስ ጨዋታ በማኒላፊሊፒንስ

በመላው አለም ተወዳጅነትን ያተረፈ የቡድን ስፖርት አይነት ነው፡፡ ጨዋታው እኤአ በ1891 በካናዳዊው ዶ.ር ጀምስ ኒስሚዝ በአሜሪካ አገር ተፈጠረ፡፡ የቅርጫት ኳስ ወይም ባስኬት ቦል፡፡ ጨዋታው በእጅ የሚከናወን ሲሆን በመሰረታዊነት የ4 መአዘን ሬክታንግል ቅርፅ ያለው መጫወቻ ኮርት 5 ተጫዋቾ ያሉት ሁለት ቡድኖች እና በእጅ የሚወረወረው ድቡልቡል ኳስ ለጨዋታው አስፈላጊ የሆኑ ቁሶች ናቸው፡፡ 5ቱ ተጫዋቾ ሁልጊዜም የተጫዋቾችን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ከተጫዋቾቹ በቁመት ረጅም የሆነው ተጫዋች አብዛኛውን ጊዜ የመሀል ቦታ ይይዛል፡፡ እኤአ በ1891 በካናዳዊው የጂም መምህር ጀምስ ኒስሚዝ በስፕንግ ፊልድ ማሳቹስትስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተፈጠረው የቅርጫት ኳስ በአሁኑ ሰአት በአለማችን ላይ እጅግ ታዋቂና በመላው አለም በርካታ ተመልካቾች ያሉት የስፖርት አይነት ነው፡፡

የናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን ለአለም ፕፌሽናል ባስኬት ቦል በማሳደግና በማስተዋወቅ በክፍያ በተሰጥኦና በውድድር ብቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቶለታል፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ውጪ ያሉ የብሄራዊ ሊግ መስፈርትን ያሟሉ ታላላቅ ክለቦች ለአህጉራዊ ቻምፒየን ሺፕ እንደ ኢሮሊግ እና FIBA አሜሪካ ሊግ የናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን አስተዋፅኦ ማሳያ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የFIBA ባስኬት ቦል ወርልድ ካፕ እና men’s Olympic basketball ውድድር ዋና ዋና የአለማቀፍ ዝግጅቶችን እና የብሄራዊ ቡድኑ በርካታ ተጫዋቾችን መሳብ የቻሉ ውድድሮች ናቸው፡፡ የሠውነት ማጎልመሻ ትምህርተ ፕሮፌሽናል በ young men’s Cristian association tinning school በአሁኑ መጠሪያው spring filed college ውስጥ አሰልጣኝ የነበሩት ካናዳዊ ጀምስ ኒስዝ እኤአ ከዲሴምበር 1891 ቀደም ብሎ የጂም ትምህር ቤት ክፍልን በዝናባማ ወቅትም ለማስቀጠል ፈለጉ፡፡ ተማሪዎቹ ክረምቱንም በተሻሎ የሰውነት ጥንካሬ እንዲያሳፉ በሚል በርካታ ሀሳቦች አስበው በኋላም ከበርካታ ሀሳቦች ውስጥ የባስኬት ቦልን በመምረጥ 10 ጫማ ወይም 3 ሜትር ከፍታ ያለው የባስኬት ቦል መረብ መስቀያ አዘጋጁ፡፡

ለባስኬት ቦል መጫወቻ ተብሎ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ኳስ ብራውን ወይም ቡናማ ቀለም ሲኖረው እኤአ በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ ግን ቶኒ ሂንክል የተባለ ሰው ለተጫዋቾቹ ግልፅ ሆና መታየት አለባት በሚል የኳሷ ቀለም ወደ ብርቱካናማ ቀለም እንዲቀየር አደረገ የተቀየረውም ቀለም እስካሁን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በ1892 ከገና እረፍት መልስ ለመጀመሪያ ጊዜ የባስኬት ቦልን የተጫወተው ፍራንክ ማሀን ሲሆን በወቅቱ ስያሜውን ምን እንደሚሉት ኒስሚዝን ጠየቃቸው እሳቸውም ውድድሩን የማስጀመር ሀሳብ እንጂ ስለስያሜው አላሰብኩበትም ሲሉ መለሱለት፡፡ ፍራንክ ለምን ኒስሚዝ ኳስ አይሉትም ሲል ሀሳብ አቀረበ፡፡ ኒሚዝም ከሳቁ በኋላ እንዲህ አይነት ስያሜዎች ጨዋታውን ይገድሉታል ብለው መለሱለት፡፡ ፍራንክም መልሶ ለምን ባስኬት ቦል አንለውም አለ፡፡ ኒስሚዝም ባስኬት አለን ኳስም አለን ስለዚህ ባስኬት ቦል መባሉ ለኔ ተስማምቶኛል፤ ጥሩ ይመስለኛል ብለው አፀደቁለት፡፡ የመጀመሪያው የባስኬት ቦል ውድድርም ኒዮርክ ውስጥ በሚገኝ YMCA ጂምዚየም ውስጥ እኤአ በጃንዋሪ 1892 በ9 ተጫዋቾ ተጀመረ፡፡ በወቅቱ የእግር ኳስ 10 ተጫዋቾ በ1 ቡድን የሚጫወቱበት ወቅት ስለነበር ሀይለኛ የበረዶ ግግር የእግር ኳስ ጨዋታቸውን እንዳያከናውኑ ስላስቸገራቸው ወደቤት ውስጥ ገብተው 10ሩ ተጫዋቾ በሁለት በመከፈል 5 5 ሆነው መጫወት ባስኬት ቦልን ወይም የቅርጫት ኳስን ጀመሩ፡፡ በ1897 -1898 በአንድ ቡድን የተጫዋቾ ብዛት 5 ሆኖ ፀደቀ፡፡

እኤአ በ1980ዎቹ እና በ1990ዎ ውስጥ ፕሮፌሽናል ውድድሮችን በማካሄድ የስፖርቱን ተወዳጅነትና እውቅና ከፍ እንዲል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ እና የምንግዜም ምርጥ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች የሚባሉት 3 ተጫዋቾ ላሪ በርድ፤ ኢረን ማጂክ ጆንሰን እና ማይክል ጆርዳን ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ ፌብርዋሪ 17፣1963 በአሜሪካዋ የኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው ማይክል ጆርዳን በአለማቀፍ ደረጃ ብዙ ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል፡፡ ብዙ ሰዎች ከምርጥ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሳይሆን መቼም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ተጫዋች ነው በማለት ያሞግሱታል፡፡

ከሴቶች እውቅ የባስኬት ቦል ተጫዋቾች ውስጥ አንዷ የሆነችው የአሜሪካ ፕሮፌሽናል ባስኬት ቦል ተጫዋች ማያ አፕሪል ሞኖር በርካታ የብሄራዊ ቻምፒየን ሺፕን በማሸነፍ የጆን ዎደን አወርድ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ እኤአ በ1932 ስምንት ሀገራት የብሄራዊ ባስኬት ቦል አሶሼሽን FYBA አቋቋሙ፡፡ ስምንቱ መስራች ሀገራት አርጀንቲና ፤ Czechoslovakia ፤ ግሪክ ፤ ጣሊያን ፤ lasiva፤ ፓርቹጋል ሮማንያ እና ሲውዘርላንድ ናቸው፡፡ ሴቶች በባስኬት ቦል ውድድር ላይ መሳተፍ የጀመሩት በ1892 በስሚዝ ኮሌጅ ውስጥ ነበር፡፡ በወቅቱ ሰንዳ በርሶን የተባለች የሰውነት ማጎልመሻ መምህር የኒስሚዝን የባስኬት ቦል ህጎች ለሴቶች እንዲሆኑ አድርጋ አስካከለቻቸው፡፡ በአጭሩ በአዲሱ ስፖርት በመማረኳ ስለውድድሩ ከኒሰሚዝ ብዙ ለመማር ትፈልግ ነበር፡፡ በመጋቢት 21 1893 የመጀመሪያው የሴቶች ባስኬት ውድድርን አዘጋጀች፡፡

  NODES
Association 1
Note 1