ዴሞክራሲፖለቲካ ሥርዓት ሲሆን ትርጓሜውም ሕዝባዊ መንግስት ማለት ነው። በሌላ አባባል ዲሞክራሲ ማለት ህዝብ የሚያስተዳድረውን አካል ያለምንም ተፅዕኖ ከመካከሉ መርጦ ሥልጣን የሚሰጥበት ሥርዓት ነው።

የዲሞክራሲ መጠን በያገሩ (2019 ዓ.ም. )
*ሰማያዊ -- በጣም ዲሞክራሲያዊ (woደ 10 የተጠጋ
*ጥቁር -- ትንሽ ዲሞክራሲያዊ (ዎደ 0 የተጠጋ)[1]
ቢያንስ በስም ዲሞክራሲያዊ የሆኑ አገሮች 2018 (አረንጓዴ); ሳውዲ አረቢያ, ኦማን, የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ, ብሩናይ, ፊጂ, እና ቫቲካን በገሃድ እራሳቸውን ዲሞክራሲያዊ እንዳልሆኑ ያውጃሉ

ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ

ለማስተካከል

ዴሞክራሲ በተጠነሰሰበት ጥንታዊት ግሪክ ፣ ሰዎች ይኖሩ የነበረበት መሠረታዊ የፖለቲካ አሃድ (ዩኒት) ፣ ከተማዊ መንግስት ይባላል። ይህ በአሁን ዘመን ካለው አገር ወይንም ብሔራዊ መንግስት ይለያል። ከተማዊ መንግስታት፣ ለምሳሌ አቴና እንደ ከተማ አስተዳደርነቱ ፣ በቆዳ ስፋት አንስተኛ ስለነበር የዘመኑ ዲሞክራሲ በቀጥተኛ ተሳትፎ (በስብሰባ) ላይ የተመሰረተ ነበር። ነገር ግን ይህ ዓይነት አሰራር ከ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ለተነሱት በንፅፅር ግዙፍ ለሆኑት ብሔረ መንግስታት እማይቻል ስለነበር (ማለት ከአገሪቱ ግዙፍ የቆዳ ስፋት አንጻር ሁሉን ዜጋ በየሳምንቱ ለስብሰባ መጥራት ስለማይቻል) በእንግሊዝ አገር ፓርላማ የተባለ አዲስ ሥርዓት ተፈጠረ። ይህም ማለት ሕዝቡ ተወካዮቹን (የፓርላማ ዓባላትን) ይመርጣል፤ ተመራጮችም መንግሥትን ይመሠርታሉ። ይህ ዓይነት ሥርዓት (ቀጥተኛ ያልሆነ ዴሞክራሲ) በመባል ይታዎቃል። በአሁኑ ሰአት አብዛሃኛዎቹ የአለም ሃገራት የሚጠቀሙበት የመንግስት መዋቅር ነው።

ዜግነትና ዴሞክራሲ

ለማስተካከል

አንድ ሥርዓት ዲሞክራሲያዊ፣ በሌላ አነጋገግር ሕዝብ ወይም ሕዝብ የቆመ ነው ከተባለ፣ ሕዝብ ማለት እዚህ ላይ ምንድን ነው? አብዛኛውን ጊዜ ሕዝብ ማለት ዜጋ ማለትን ሲዎክል፣ እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አብዛኞች ዲሞክራሲያዊ ሃገሮች ዜግነትን ትንሽ ለሆነ የህብረተሰብ ክፍል (ሴቶችን፣ ድሆችን፣ ዘሮችን ያገለሉ) ብቻ ያድሉ ነበር። እነዚህ ትንሽ ክፍሎች ብቻ እሚሳተፉበት ዴሞክራሲ በአሁኑ ዘመን ተቀባይነትን ያጣ ነው። ባሁኑ ዘመን፣ ዲሞክራሲ ማለት ብዙኃኑ ኅብረተሰብ መንግሥት የማዋቀር መብት አለው። የጥቂቶች መብት ደግሞ በህግ የተጠበቀ ነው።

ሥርዓተ ሕዝብ፣ ሥርዓተ ልሂቅ፣ ሥርዓተ ጥቂት

ለማስተካከል

ፖለቲካዊ ዜግነት ሕጻናትን እንደማይጨምር አሁን ድረስ አብዛኞች ሃገራት የሚሰሩበት ነው። ይሁንና፣ በዚህ መንገድ አላግባብ ሌሎችም የሕዝብ አካላት እየተገለሉ ሄደው፣ ዴሞክራሲው ወደ ሌላ ዓይነት ሥርዓት ሊቀየር ይችላል። ለምሳሌ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ የተከበሩ ሰዎች ብቻ እሚሳተፉበት ሥርዓት ሲፈጠር ሥርዓተ ልሂቅ ወይንም አሪስቶክራሲ ይባላል። በሆነ አጋጣሚ ዕድል አግኝተው ጥቂት ቡድኖች ብቻ በማህበረሰቡ ላይ በሚተላለፉ ውሳኔዎች ሲሳተፉ ሥርዓተ ጥቂት ወይንም ኦሊጋርኪ ይባላል። ይህን ሁኔታ ለማዎቅ አንድ አንድ ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሥርዓት ሳይቀር፣ ጊዜ አግኝተው በፖለቲካው የሚሳተፉ ግለሰቦች ከአጠቃላይ ዜጋ ጥቂት ስለሆኑ። ይሁንና በዲሞክራሲ፣ የመሳተፍ መብቱ ለሁሉም ዜጋ ምንጊዜም ያለ ነው፣ ይጠቀሙበት አይጠቀሙበት።

ዴሞክራሲ ለምን ተፈለገ?

ለማስተካከል

እንደ ፈላስፋው ጆን ስቱዋርት ሚል ሦስት ምክንያቶች ይጠቀሳሉ[2]

ሕግ አርቃቂዎች የአንድን ሕብረተሰብ ጥቅም፣ መብት እና አስተሳሰብ በሚያረቁት ሕግ ውስጥ ግምት እንዲያስገቡ ከሌሎች የፖለቲካ ሥር ዓቶች በላይ ዴሞክራሲ ያስገድዳቸዋል። በዚህ ምክንያት ሰዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ የመጎዳታቸው ዕድል አንስተኛ ነው። ተመራማሪ ዓማርትያ ሴን ዋቢ ሲሰጥ «በማናቸው ዲሞክራሲያዊና ሉዓላዊ መንግስታት ከፍተኛ ርሃብ ተከስቶ አያቅም» ይላል።

ዴሞክራሲ አብዛኛውን ሕዝብ በውሳኔ አስጣጥ ላይ ስለሚያካፍል፣ ከሌሎች የፓለቲካ ሥርዓቶች በበለጠ ሥለ ሕዝቡ ጉዳይ ያዎቀ ሆኖ ይገኛል። በውሳኔ አሰጣጥ የሚካፈለው ሕዝብ መብዛት በሌላ ጎን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እሚደረገውን ስራ ያግዛል፣ ተሳታፊዎችም ስለ ጉዳዮች የበለጠ የተተቸና የተብራራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል።

የዜጎችን ባሕርይ የማሻሻል ምክንያት

ለማስተካከል

በዴሞክራሲ ሥርዓት ያሉ ሰዎች በውሳኔዎች ላይ ስለሚሳተፉ፤ ከሌሎች ሥርዓት ሰዎች በተለየ እራሳቸውን ችለው እንዲያስቡ፣ በሃሳባቸው ምክንያታዊ እንዲሆኑ እና የሌሎችን መብቶች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ስለሚገደዱ በሥነ ምግባር እንዲሻሻሉ ይሆናሉ።

ከሚያስከትለው ጥቅም ውጭ ሌሎች ሥነ ምግባራዊ ጥቅሞች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ ሓርነት እና ዕኩልነት፣ እኩልነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመናገር መብት፣ ፍትህ ይጠቀሳሉ

በዴሞክራሲ ላይ የተነሱ ትችቶች

ለማስተካከል

ፕላቶሥርዓተ ልሂቃን ዓይነት መንግስት ደጋፊ ስለነበር ዲሞክራሲን ከዚህ አቋሙ ተነስቶ ለመንቀፍ ሞክሯል። በእርሱ አስተሳሰብ በዲሞክራሲ ሥር ዓት ወደ ሥልጣን ላይ መውጣት እሚችሉት የምርጫ ሥር ዓቱን በማጭበርበር ወይንም በብልጥ ንግግር እና ስራ ሰውን በማታለል የተካኑ ሰዎች ይሆናሉ። ምርጫን እሚያሸንፉ ሰዎች ደግሞ የግዴታ መንግስታዊ ኣስተዳደር ላይ ብቁ ሆነው ስለማይገኙ፣ ዴሞክራሲ መንግስትን ለንደዚህ ያለ ግሽበት ይዳርጋል ይላል።

የእንግሊዙ ቶማስ ሆብስ በአንጻሩ የዘውድ ሥርዓትን በመደገፍ፤ የዴሞክራሲ ሥርዓት መንግስት እንዳይረጋጋ እሚያረጉ ተቃውሞዎችን ያበረታታል በማለት ይነቅፋል።

የዴሞክራሲ ተቋሞች

ለማስተካከል

ምርጫ ተቋም

ለማስተካከል

ዴሞክራሲ የመጣው የግሪክ ቃል ከሆኑት «ዴሞስ» ማለት «ህዝብ» እና «ክራቶስ» ማለት «ስልጣን» የመጣ ቃል ነው። በጥንታዊ የግሪክ ከተማ አቴንስ አገዛዝ ይተገበር ነበር።


ዋቢ ጽሑፎች

ለማስተካከል
  1. ^ "Democracy Index 2017 - Economist Intelligence Unit".
  2. ^ Christiano, Tom, "Democracy", The Stanford Encyclopedia of Philosophy (Fall 2018 Edition), Edward N. Zalta (ed.), forthcoming URL = <https://plato.stanford.edu/archives/fall2018/entries/democracy/>.
  NODES
Done 1
see 1