?ገመሬ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ሰብአስተኔ
አስተኔ: ዘረሰብ Hominidae
ወገን: ገመሬ Gorilla
ዝርያ: 2 ዝርያዎች

ገመሬ (ጎሪላ) አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ አጥቢ እንስሳ ነው።

ገመሬ በጣም ትልቅ የጦጣ አይነት ነው።

በኢትዮጵያ አነጋገር ደግሞ «ገመሬ» ማለት የዝንጀሮች አለቃ ዝንጀሮ ሊሆን ይችላል።

በ478 ዓክልበ. የቀርታግና ንጉሥና መርከበኛ ተጓዥ 2 ሓኖ እስከ ጋቦን ድረስ እንደ ጎበኘ ይታስባል፤ እሱም እንደ ዘገበው በዚያ በአንድ ደሴት በግሪክ «ጎሪላይ» የተባለ በፍጹም ጠጉራምና አውሬ ጎሣ እንዳገኘ ጻፈ፤ ቆዳዎችንም ይዘው ወደ ቀርታግና ተመለሱ። እነኚህ የሰው ልጆች ሳይሆኑ ጦጣዎች እንደ ነበሩ ስለሚታመን፣ ዘመናዊው የጦጣ ወገን ስም «ጎሪላ» (Gorilla) ከዚህ ታሪክ የተወሰደ ነው።

የእንስሳው ሳይንሳዊ ጸባይ

ለማስተካከል

የገመሬ ወገን ሁለት ዝርዮች አሉት፣ በየዝርያውም ሁለት ሁለት ንዑስ ዝርያዎች አሉ። የገመሬ ወገን አባላት፦

አስተዳደግ

ለማስተካከል
 
ሁለቱ ዝርዮች፦ ምዕራብ ገመሬ እና ምሥራቅ ገመሬ

እንደ ሌሎች ጦጣ አይነቶች ሳይሆን፣ ገመሬ በመሬት ይውላል ይተኛልና ከፍራፍሬ ይልቅ በብዛት ቅጠላቅጠልን፣ ግንደ ብሌንም ይበላል። ደግሞ ምስጥጉንዳን ይበላል። ገመሬዎች ሁሉ ከሌላ ጦጣ አይነቶች ይልቅ እጅግ ቦርጫም ናቸው። የሚበሉት ሓመልማል ብዛት ስለሚበቃቸው፣ ብዙ ውሃ አይጠጡም። ገመሬን የሚበላው ዋና ነጣቂ ግሥላ ነው።

ያደገው ወንድ ጎሪላ አለቃ የብር ቀለም ጀርባ ስላለው «ብር-ጀርባ» ይባላል። ባብዛኛው ጊዜ ገመሬዎች ሰላማዊ ናቸው፣ አንድ ገመሬ ሲቆጣ አትክልት ይጥላልና ደረቱን ይደብድባል። አልፎ አልፎ ግን ብር-ጀርባዎች ለቡድኑ አለቃነት እርስ በርስ እስከ መግደል ድረስ ይታገላሉ።

በጣም ትንሽ የእጅ ምልክት ቋንቋ ለመማር በቂ ብልሃት እንዳላቸው ተመራማሪዎች አሳውቀዋል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር እና ብዛቱ

ለማስተካከል

የእንስሳው ጥቅም

ለማስተካከል
  NODES
Note 1