1 ሐቱሺሊ ምናልባት 1559-1536 ዓክልበ. አካባቢ ከ1 ላባርና በኋላ በኩሻራና በሐቱሳሽ (በሐቲ) አገር) የገዛ ንጉሥ ነበር።

የላባርና (1)፣ የ1ሐቱሺሊ (2፣ ክፍት ብጫ)ና የተለፒኑ (3) ግዛቶች ስፋት ያህል

1 ሐቱሺሊ አዋጅ ማዕረጉ «ታባርና» ነው፣ ልጆቹን ላባርናና ሁዚያን ስለ ጭካኔያቸው ከወራሽነት ሽሯቸው 1 ሙርሲሊን ወራሹን ያደርገዋል። አያቱም ሕሽሚ-ሻሩማ እንደ ሆነ ይጠቅሳል። በሌላ ሰነድ የንግሥቱ ስም ካዱሺ ተዘረዘረ።

የሐቱሺሊ ዜና መዋዕል ከዘመኑ ስድስቱን አመታት ይገልጻል። በዚህም ውስጥ የ፩ ላባርና ንግስት ታዋናና ወንድም ልጅ መሆኑን ይጠቅሳል።

  1. .፦ ሐቱሺሊ ሻናኊታን ከበበ፣ ዙሪያውን አጠፋ፣ ዛልፓን አጠፋ፣ አራት ሠረገሎችና ሌሎች ስጦታዎች ለጣኦታት ሰጠ።
  2. .፦ ሐቱሺሊ ወደ ሶርያ ገብቶ የያምኻድ ንጉሥ 3 ሃሙራቢ ተገዥ የሆነውን የአላላኽ ገዥ አሚታቁ አሸንፎ አላላኽን አጠፋ። ከዚያ ሐቱሺሊ የኡርሹ ሑራውያንን አሸነፋቸው፣ ያምኻድና ከርከሚሽ ረድኤታቸውን ለኡርሹ ምንም ቢሰጡ።[1]
  3. ፦ ሐቱሺሊ ወደ ምዕራብ ወደ አርዛዋ አገር ገብቶ ከብትና በግ ወሰደ። ይህ እየሆነ በምሥራቅ ያሉት ክፍሎችና ሑራውያን እንደገና ስለገቡበት ተመልሶ አመጹን በማጠፍ ዘመተ።
  4. ፦ ሐቱቪሊ ወደ ስሜኑ ተመልሶ ሻናኊታንና የዙሪያውን ከተሞች አጠፋቸው።
  5. ፦ ሐቱሺሊ ወደ ሶርያ ተመልሶ ያምሓድንና ኢሱዋን በደብረ አታሉር ውግያ አሸነፈ፣[2] ኤፍራጥስ ወንዝን ተሻግሮ ኢሡዋንና ሌሎችንም የሖርያውያን ከተሞች አጠፋቸው፣ ብዙ ብርን ዘርፎ ወደ ሐቱሳሽ ላከ።

በ1300 ዓክልበ. በኬጥያውያን ንጉሥ 2 ሙዋታሊዊሉሳ ንጉሥ አላክሳንዱ ጋራ በተዋዋለ ስምምነት እንደሚተርክ፣ የቀድሞ ንጉሥ «ላባርና» አርዛዋንም ዊሉሳንም እንደ ያዘ ሲል ምናልባት 1 ሐቱሺሊ («2 ላባርና») ማለቱ ይሆናል። ሐቱቪሊ ሐለብን ከያምኻድ ግን መቸም አልያዘምና ምናልባት በሐለብ ዘመቻ እያለ ተቆስሎ ሞተ። ይህ ተከታዩ ሙርሲሊ «የአባቴን ደም ቂም በማብቀል» ያምኻድን እንዳጠፋ ስለ ዘገበ ነው።[3][4]

ቀዳሚው
1 ላባርና
ሐቲ ንጉሥ
1559-1536 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 ሙርሲሊ
  1. ^ William J. Hamblin (2006). Warfare in the Ancient Near East to 1600 BC. p. 289. ISBN 9781134520626. http://books.google.nl/books?id=biyDDd0uKGMC&pg=PT289&dq#v=onepage&q&f=false. 
  2. ^ Trevor Bryce (1999). The Kingdom of the Hittites. p. 83. ISBN 9780199240104. http://books.google.nl/books?id=Agg5-lpVI2MC&pg=PA83&dq=#v=onepage&q&f=false. 
  3. ^ Trevor Bryce (2014). Ancient Syria: A Three Thousand Year History. p. 29. ISBN 9780191002922. http://books.google.nl/books?id=q8Z7AgAAQBAJ&pg=PA29&dq#v=onepage&q&f=false. 
  4. ^ Charles Burney (2004). Historical Dictionary of the Hittites. p. 107. ISBN 9780810865648. http://books.google.nl/books?id=azPl5Jzv930C&pg=PA107#v=onepage&q&f=false. 
  NODES
Note 1