ዋና ገጽ

እንኳን ወደ ዊኪ መዝገበ ቃላት በደህና መጡ



Wikimedia Foundation ባለ ብዙ ቋንቋ ነጻ መዝገበ ቃላት

ዛሬ ዐርብ 27 ዴሰምበር 2024 ነው። እስከ አሁን እዚህና 3,495 አባሎች አሉ


አዲስ ገጽ ፍጠር/ሪ





ዊኪ-መዝገበ-ቃላት የባለ ብዙ ቋንቋው ዊክሽነሪ የአማርኛ ዝርያና የ ዊኪፒዲያ ነፃው መዝገበ-ዕውቀት እህት መርሃ ግብር ነው። ዓላማውም ሁላችንም በመተባበር አንድ ክፍት ነፃና ሁሉም ሰው ያለ ምንም ገደብ ሊጠቀምበት የሚችል መዝገበ-ቃላትን መድረስ ነው። ይህ የኣማርኛ ዊኪ-መዝገበ-ቃላት በማርች 23 2006 ተጀምሮ በአሁኑ ሰዓት 2,455 ገጾችን ይዟል። አንድ ገጽ የአንድ ቃልን ምንጭ፣ ሂደታዊ ታሪክን፣ የቀድሞና ወቅታዊ አጠቃቀምን፣ ተዛምዶን፣ የአጠቃቀም ምሳሌን፣ ተጨማሪ ተጠቃሽ መረጃዎችን፣... ወዘተርፈ ይይዛል። ይህ መዝገበ ቃላት አማርኛን እንደ ማዕከላዊ መነሻ ቢያደርግም በዓለም ላይ ያሉ ቋንቋዎችን ሁሉ ቃላት ማካተት ይቻላል። ይህ ከላይ ሲመለከቱት አስቸጋሪና መዝገበ ቃላቱን ስርዓት የሚያሳጣው ሊመስል ይችላል። ይህ የሚመስለን በባሕላዊው ኅትመት ላይ የተመሠረተ የመዝገበ ቃላት አጠቃቀምን ስለምናስብ ነው። የዓለም ቋንቋዎችን ሁሉ በአንድ መጽሐፍ ላይ እናስቀምጥ ብንል የማይቻል ነው። ለመቀምር (Computer) ምስጋና ይግባውና የዕውቀትና የጊዜ ገደብ ካልሆነ በስተቀር ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ገደብ እዚህ ላይ አይኖርም።

የሚያውቁት ቋንቋ ካለ፥ ኦሮምኛ፣ ከምባትኛ፣ ኑዌር፣ ወላይትኛ፣ አገውኛ፣ ትግርኛ፣ ጃፓንኛ፣ ህንድኛ፣ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ኖርዌጅኛ፣... ወዘተርፈ ቃሉን ጽፈው ከየት እንደመጣ፣ ትርጉሙን፣ ተጠቃሽ መረጃዎችን... ወዘተርፈ ማስቀመጥ ይችላሉ። የየትኛውንም ቃል የአማርኛ ትርጉም ለማወቅ የፈለገ ተጠቃሚ ሁሉ ወደዚህ መጥቶ ማየት ይችላል ማለት ነው። በተለይ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ቋንቋዎች ቃላት እንደ ማከማቻና አንዱ ከአንዱ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደማሳያ ሊያገለግል ስለሚችል የሚያውቁትን ቃላት በሙሉ በማስገባት ትርጉማቸውን ያስቀምጡ።

የመቀምር (Computer) ቃላት ትርጉም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የመቀምር (Computer) መድብለ ቃላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ICT glossary at AAU ይገኛል፡፡ ይህ ከ2500 ቃላት በላይ የያዘው መድብለ ቃላት የመቀምር (Computer) ኣግባሪፅፎችን (programmes) ለመተርጎም የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል። ጥረቱ በቀላሉ የሚሻሻል ሁለት ችግር አለበት።

  1. ተጠሪው (server) በጣም ቀሰስተኛ ስለሆነ ለተጠቃሚው በጣም አስቸጋሪ ይሆናል። ይህ መስተዋት ገጽ (mirror site) በተለያዩ ክፍለዓለማት በማስቀመጥ ማሻሻል ይቻላል።
  2. ገጹ ላይ የተሰጠው የexel ቅጂ የተጻፈው በተለያየ ገጸቀለም/መልክዓፊደል (font) ከመሆኑም በላይ አንዱ ከአንዱ ጋር ተኳዃኝ (compateble) አይደለም። በዩኒኮድ ደረጃን የጠበቁ ነፃ ፊደሎች በመጠቀም ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊያገኘው በሚችልበት ሁኔታ ቢዘጋጅ ጠቃሚነቱ ከፍተኛ ይሆናል።
የአቡጊዳ ታሪክ

የአማርኛ ቋንቋን የምንጽፍበት ፊደላት ታሪክን ከአቡጊዳ በዊኪፒዲያ ይማሩ።

የመቀምር (Computer) ቃላት ትርጉም

ይህንን የመቀምር (Computer) መድብለ ቃላት computer terms glossary አጓዳኝ ሲጫኑት 1500 የሚጠጉ የመቀምር (Computer) ቃላትን የእንግሊዝኛ-አማርኛ ትርጉም ረቂቅን ያገኛሉ። ይህን መድብለ-ቃላት ወደ መቀምር (Computer) መድብለ ቃላት ክፍል በማዛወር ላይ እንገኛለን። እነዚህ ትርጉሞች ረቂቅ ሓሳቦች እንጂ የመጨረሻ አይደሉም። እርስዎ የተሻለ አማራጭ አለ ብለው ካሉ ይህንን አማራጭ ወይም አማራጮች ከመጀመሪያው ትርጉም ጎን በነጠላ ሰረዝ በመከፋፈል ያስቀምጡት። የመጨረሻ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ አማራጮቹ ሁሉ ተዘርዝረው ቢገኙ የተሻለውን አማራጭ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመስጠት ያመቻል።


በቅርቡ በማይክሮሶፍት ውጤቶች ላይ የተመረኮዘ ባለ 2828 ቃላት የመቀምር (Computer) መድብለቃላት በEICTDA ተለቅቋል። መድብለ ቃላቱ የተሟላና ጥራት ያለው ነው ለማለት ቢያስቸግርም ለተርጓሚዎች እንደ መነሻ ሊያገለግል ስለሚችል እዚህ ቀርቧል። በዚህ አጋጣሚ የባለሥልጣኑ ተርጓሚዎች፣ ከዚህ ቀደም በባለሙያዎችና ተጠቃሚዎች የተሠሩ ብዙ የትርጉም ሥራዎች ስለ ኣሉ እነሱን እያዩ ከባለሥልጣኑ የሚወጣውን ሥራ ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ቢጥሩ ጥሩ ነው። ይህ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ሥራ በመሆኑ በማን ኣለብኝነት ጥራት የሌለው ሥራ መስራት ጥሩ አይሆንም። ለመጠቀም ያመች ዘንድ ከላይ የተጠቀሰው በዚሁ ዊክሽነሪ EICTDA መድብለቃላት ውስጥ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት መዝገበቃላት አስራር ላይ የተመረኮዙ ጥናቶች ላይ ያተኮረ ጉባዔ.......


ማስተዋፅዖ ይችላሉ!
ይህ መዝገበ-ቃላት የሚፃፈው በፈቃደኛ አስተዋፂዖች ነው። ማስተዋፅ በጣም ቀላልና ማንም ሰው ሊያደርገው የሚችለው ነው። «አርም» የሚለውን በመቀጭቀጭ ሥራዎን መጀመር ነው። አንድ ቀይ አጓዳኝ ማለት ገቢ ቃሉ ዊኪ-መዝገበ-ቃላቱ ውስጥ ገና የለም ማለት ነው። አዲስ ገቢ ቃልን በመፈለጊያ ሳጥን ውስጥ ጽፎ «ሂድ» በማለት መፍጠር ይቻላል። በተጠቃሚነት መመዝገብም ይቻላል። ርዳታ ካስፈለገዎትም ምክር ቤቱን ይመለልቱ

ሰዋሰው
የዘይቤ መመሪያ

ዊክሽነሪ ዊኪፒዲያ አይደለም
ስለዚህ የመዝገበ-ዕውቀት መጣጥፎችን እዚህ ላይ አያኑሩ።



Language
  NODES
Note 1